Tuesday, February 7, 2012

 ራሰ በራው ሜዳችን


ባለፉት ኣመታት የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ኳስ ሜዳ የኮረዳ ደረት ይመስል ጉች ጉች ባሉ የሳር ጉቶ ጡቶች የተሞላ ነበር፤ ታዲያ የሾሉ ቀንዳም ጡቶቹን ኣይቶ ያልማለለ ተጫዋችና ኳስ ኣልነበረም። ጡት ናፍቆት ዘው ያለ እግሩን ሰበረ፤ ጠልፎት የወደቀ የጡት ኣምሮቱን ጨረሰ፤ ምን ኣደከመህ ብዙ ብዙ ታሪክ ተሰርቶበት ነበር ታዲያ ሜዳው ይሉንኝታ ባይኖረው እንጂ ዛሬ ብቻዉን የቀረው። ስንቱ ስንቱ ከጡት የመጋጨት ኣባዜ ያናዎዛቸው ኳስ ኣባራሪ እና ተባራሪ ኳሶች ከጉቶ እየተላተሙ እንዳልተገራች በቅሎ በየኣቅጣጫው ይነጥሩ እና ይዘሉ ነበር።ይግረመህ እና ኳስ መታሁ ብሎ ጡት የመታ ተጫዋች ነጥሮ ተመልካች መሃል ወድቆ ዳኛው[በማዘን_ ያቀዋላ የጡትን ኣምሮት ሂሂሂ] ለተቃራኒ ቡድን እንደእጅ ዉርወራ ኣድርገው እንዲያስገቡት ትእዛዝ ሰጥተው ምስኪን የጡት ኣፍቃሪው ተመልሶ ቡድኑን መቀላቀል ቻለ። 
 
 
 
 
 
ይሄ የጡት ፍቅር ታዲያ ያን ግዜ ኣለ የተባለ መቦዘኛ ቦታ ሆነ፤ እናልህ ሰራተኛውም ተማሪውም ዉሎ አዳሩን ኳስ ሜዳ ማድረጉ ያሳሰበው የግቢው የመዝናኛ እና የመሳሰሉት ኣስተባባሪ ክፍል ጉዳዩ እንዲጠና በጠየቀው መሰረት የሴዳክሽን ትምህርት ክፍል ምክንያቶቹ የሜዳዋ ጡቶች መሆናቸዉን ጠቁሞ ዉጤቱን ሲያቀርብ ኣስተባባሪው የጡቶቹን መጥፋት ጥሩ ኣማራጭ ሆኖ ስላገኘው ሜዳዋ የሚለው ስም ቀርቶ ሜዳው እንዲሆን ጾታው እንዲቀየር እና ጡት ሳይሆን ደረት ብቻ እንዲኖረው የሚል ዉሳኔ ላይ በመድረሱ ብዙ ሚሊዮን ብር በጅቶ የጾታ ለውጡ በፕላስቲክ ሰርጀሪ እንዲካሄ ደመደመ። ጥሩ ዶክተር ጠፋና ጊዜው በመርዘሙ የጾታ ሳይሆን የነብስ ቅየራ ኣስመሰለው እንጂ ኣይይይይይ።እናም የዉሳኔው ኣፈጻጸም በብዙ ኳስ ኣባራሪዎች የኣጀብ እይታ ተከቦ እና በኮንቲንር ዉስጥ ታጭቀው ጉንጫቸው በእንባ ጅረት በሚታረሱ ኳሶች ዋይታ ታጅቦ ተጠናቀቀ። ከዚያ ወዲህ ጭለማዉን እየጠበቀ የሜዳዉን ዙሪያ ከቦ ይጎነትላል እንጂ የድሮው በቀን ሜዳ ነው እያሉ ጡት መጎንተል ሃላል መሆኑ ቀረ [የማታዉን ኣትጠይቀንኝ ሆ ሆ]። በል በቀጣዩ ግዜ የፕላስቲክ ሰርጀሪውን ኣስመልክቶ እናወጋለን። ደህና ሁንልኝ።ኣይይይ በል ጀንደሮች እንዳይሰሙኝ (ኣንተ ነህ ጡት ወዳጁ ብየ ነው) ለሌላ ኣታሳይ ሆ ሆ ደግሞ ሴቶችን ያላሳተፈ ጽሁፍ ነው ብለው አንዳይከሱኝ ሂሂሂ።


Views of ADO: Strives for ease in information sharing for development

No comments:

Post a Comment