Sunday, January 29, 2012

ትከናነበው የላት.....

 ሰሞኑን '' ቆሻሻየን ሜዳ መጣል ቢደብረኝ፣ 
ሆድ ዕቃ በሌለው ገንዳ ዉስጥ ጨመርኩኝ።"
ከታች እንደምትመለከቷት ማለት ነው። ይቺ ገንዳ ባንድ በኩል "ንፁህ አካባቢ እንፍጠር" ስትል በጀርባዋ ደግሞ "ቆሻሻዎን ይስጡኝ" የሚሉ የወግ-አምብቅ ምላሷን ይዛ ከግብርና ኮሌጅ ወደ ሂሩት ሬስቶራንት በምወስደው መንገድ ከትልልቅ አፍንጫ ሰባሪ ማአዛ ካላቸው ክፍት አፍ የቆሻሻ ገንዳ ዘመዶቹአ ጋር ተሰድራ የሰው ቆሻሻ  ትፈልጋለች። እናም የራሷን ቆሻሻ ሜዳ እየበተነች የእናንተን አምጡ፣ ሜዳ እንዳትጥሉ ማለቷ ኃላፊዎቻችንን  አስታወሰኝ። ፀረ-ሙስና አስተባባሪ ተብለው ዛሬ ስንቱ በሙስና ታስሯል ፣ የህዝብ ደህንነት የተባሉት ፖሊሶቹ ማታ ማታ የህዝብ ስጋት ናቸው /መጠጥ ላይ ከተገኘሕ አለቀልህ/።


ፖለቲካ  እስካለ እጅም እስካልዛለ፣
ሕግ አዉጭ ይፅፋል ፣
ህዝብን የሚታዘብ ሕግ አስፈፃሚ አለ ፣
ዱላዉም ቅርብ ነው ላንገራገር ላለ።

ሕጉ ለተራው ነው ለሚተዳደረው ፣
አዉጭ እና አስፈፃሚ አስተዳዳሪ ነው ፣
ያወጣዉን ህግም ሲያሻው ሰርዞ 
ሲያሻው ገንጥሎ 
ድራሹን አጥፊ ነው!

ማን አለበት !!
Legal crime!


Views of ADO: Strives for ease in information sharing for development

No comments:

Post a Comment